ታሪክ
አወቃቀር
አፈ-ጉባኤዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ሥልጣንና ተግባር
ህጋዊ መሠረቶች
ህግ መንግስት
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 251/1993
የስብሰባና የስነስራት ደንብ
ሌሎች
ቋሚ ኮሚቴዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች 
ህገመንግስታዊ ትርጉም 
የህገመንግስትና የክልል ጉዳዮች
የገቢዮችና ድጎማ ጉዳዮች
ሌሎች
በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች
ስትራቴግክ እቅድ
ቃለ-ጉባኤ
ሪፖርት
ህትመቶች
ፎርሞች
ዜና
ጨረታ
ማስታወቂያ
መልስ
የፎቶ ማህደር
ጠቃሚ አድራሻዎች
 
   

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 3ኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ አመት የስራ ጊዜ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

  • በትምህርት ሽፋን ከፍተኛ ውጤት መገቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለጹ

 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባለፉት ስድስት ወራት የምክር ቤቱን አቅም የማጠናከር በሕዝቦች መካከል ዴሞክራሲያዊ አንድነት ስር እንዲሰድ የማድረግና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን የሚያስጠብቁ ተግባሮችን ማከናወኑን አስታወቀ። ተሻሽሎ በቀረበው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አደረጃጀት አሰራርና የሥነ ምግባር ደንብ እንዱሁም በበጀት ማከፋፈያ ቀመር ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አጽድቋቸዋል።

በምክር ቤቱ በሦስተኛው የፓርላማ ዘመን ሁለተኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ደግፌ ቡላ ባቀረቡት የ1999 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት ምክር ቤቱ አቅሙን የማጠናከር በሕዝቦቸ መካከል ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ የማድረግ፣መንግስት ከሚመድበው ሀብት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆንና ፍትሐዊ አሰራር እንዲሰፍን የሚያስችል የድጎማ ቀመር የማዘጋጀት ተግባሮችን አከናውኗል።

ምክር ቤቱ የሕዝቦቸን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለማጠናከር የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ማድረጉ ካከናወናቸው ተግባሮች በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን አፈ ጉባኤው አስታውቀዋል።በዓሉ ከሀገር ውጪ በ20 ሀገሮች መከበሩም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲቀራረቡ በር መክፈቱን ጠቁመዋል።

በጎተራ አካባቢ የሚገነባውና የትራፊክ ሂደትን ለማቀላጠፍ ዓይነተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክተው መንገድ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦቸ አዳባባይ እንዲሆን የአዲስ አበባ ጊዜያዊ አስተዳደር መሰየሙን አስታውሰው በዓደባባዩ ላይም የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድነት፣ ሕብረት፣ ፍቅርና መቻቻል የሚያንፀባርቅ ሐውልት ለማሰራት ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።የምክር ቤቱ አባላት ለዚህ ሥራ መሳካት ዓደባባዩን ከማስተዋወቅ ጀምሮ የበኩላቸውን እንዲያደርጉም አፈ ጉባኤው ጥሪ አቅርበዋል።

የፌዴራል መንግስት ለክልል መንግስታት የበጀት ድጋፍ የሚሰጥበትን ቀመር ለማዘጋጀት በምክር ቤቱ ፅሕፈት ቤት ሥር አንድ ተቋም ለማደራጀት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ተቋሙ አስኪመሰረት ድረስም ባሉት አነስተኛ ባለሙያዎች በአጭር ጊዜ ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል።

የቀመሩ ዝግጅት ግልጽነት እንዲኖረው የክልሎችንም ተሳትፎ በቀጥታ ለማረጋገጥ ሲባል ከየክልሎቹ የተወጣጡ ባለሙያዎችን ለማካተት ጥረት መደረጉን ገልጸው፣ በዚህም መረጃዎችን በማሰባሰብና በተጨባጭ የክልላቸውን ሁኔታ በመግለጽ ረገድ ጠቃሚ ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል። ሥራው ሁሉንም ባለድርሻዎች ባሳተፈ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ ተአማኒነተንና ግልጽነትን ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

በምክር ቤቱ ውስጥ እስካሁን 67 ብሔሮች፣ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና እንዳገኙ አፈ ጉባኤው ጠቁመው የጽሕፈት ቤቱ ባለሙያዎች ከክልል ምከር ቤቶች ጋር በመተባበር በተደረገው ጥናት ሌሎች 10 ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና ለማግኘት የሚያስችለውን መስፈርት ያሟላሉ በሚል ለሕገ መንግሥትና ክልል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ገልጸዋል።� የአባላት ሥነ ምግባር ደንብም በሕገ መንግስትና ክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ውይይት እንደተደረገበት አመልክተዋል።

ምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤቱን መልሶ በማደራጀትና በአቅም ግንባታ ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት እንዳሉ ጠቁመው ለቀጣይ ትውልድ የሚተላለፍ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነትና ማንነት የሚያንፀባርቅ ጥናትም በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ በሚቀጥለው ዓመትም በአቅም ግንባታ የሕገመንግስት ቅጂዎችን በማሳተም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ክልሎች እንዲሰራጩ የማድረግ ዕቅድ መያዙን ጠቁመው፣ ለክልሎች የሚሰጠው የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ዝግጅትንም በየዓመቱ በማሻሻል ላይ ተኩረት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።በተጨማሪም የጋራ ገቢዎች በፌደራልና በክልሎች መካከል የሚከፋፈሉበትን ቀመር ማዘጋጀትና ማስወሰን ከተጠቀሱት ዕቅዶች ውስጥ ጥቂቶቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል በበኩላቸው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት የትምህርት ፖሊሲውን መሠረት በማድረግ በወጡት የልማት ፕሮግራሞች በትምህርት ሽፋን ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን ጠቁመው በ1983 ዓ.ም 10 በመቶ የነበረው የአንደኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን 91 ነጥብ ሦስት በመቶ ወይም 14 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸዋል።

በ1983 ዓ.ም ስድስት በመቶ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መጠን አሁን ወደ 33 በመቶ መድረሱን አመልክተው በቴክኒክና ሙያም የኮሌጆች መጠን መጨመሩንና ዓመታዊ ቅበላውም ከ100ሺ በላይ መድረሱን ጠቁመዋል።በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የነበሩ ሁለት ዮኒቨርስቲዎች ዛሬ ወደ 21 መድረሳቸውን ዓመታዎ ቅበላውም ከሦስት ሺ ወደ 41ሺ መድረሱን አመልክተዋል።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ክልላዊ ስርጭትን በተመለከተ አዲስ አበባን፣ አፋርንና ሱማሌን እንዲሁም ሌሎች ክልሎችን በሦስት ከፍሎ ማየት እንደሚገባ ጠቁመው ከእነዚህ ውስጥ የአፋርና የሶማሌ የትምህርት ሽፋን ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱን ገልጸዋል።በእነዚህ ክልሎች የትምህርት ሽፋንን በመጨመር የሚያስችል ረቂቅ ስትራቴጂ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በየክልሉ ዮኒቨርስቲዎችን የማቋቋሚያ መስፈርት ምን ነበር?በሚል ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳው ጥያቄም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመገንባት መመዘኛው ለተቋማቱ የሥራ ሂደት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምክር ቤቱ ተሻሽሎ በቀረበው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አደረጃጀት የአሠራርና የሥነ ምግባር ደንብን እንዲሁም የበጀት ማከፋፈያ ቀመር ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አጽድቋቸዋል።

 
   
     
tomtop | homekit | JJPRO X5 | LEMFO LEM7 | Vernee T3 Pro | Anet | ILIFE V7s | koogeek | DJI Mavic Air | Hubsan Drone | Wltoys | Feiyu | Zeblaze | hubsan h501s | lixada | hohem gimbal