ታሪክ

 

አወቃቀር

 

አፈ-ጉባኤዎች

 

አባላት

 

የስነምግባር ደንብ

 

ሥልጣንና ተግባር

 

ህጋዊ መሠረቶች

 

 

ህግ መንግስት

 

 

ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 251/1993

 

የስብሰባና የስነስራት ደንብ

 

 

ሌሎች

 

ቋሚ ኮሚቴዎች

 

 

አባላት

 

 

የስነምግባር ደንብ

 

ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች 

 

 

ህገመንግስታዊ ትርጉም 

 

የህገመንግስትና የክልል ጉዳዮች

 

 

የገቢዮችና ድጎማ ጉዳዮች

 

 

ሌሎች

 

በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች

 

ስትራቴግክ እቅድ

 

ቃለ-ጉባኤ

 

ሪፖርት

 

ህትመቶች

ፎርሞች

ዜና

ጨረታ

ማስታወቂያ

መልስ

የፎቶ ማህደር

ጠቃሚ አድራሻዎች

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፌዴሬሸን ምክር ቤት አመሠራረት

 

 

የፌዴሬሸን ም/ቤት በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 53 ከተቋቋሙት ከሁለቱ የፌዴራል ም/ቤቶች አንደኛው ሲሆን በአንቀፅ 61 መሠረት የፌዴራል መንግስቱን ከመሰረቱት አባል ክልሎች በሚገኙ ብሄር- ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሚወክሏቸው ተወካዮች የሚመሰረት ምክር ቤት ነው፡፡የፌዴሬሽን ምክረ ቤት በ1987 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ላይ ሲመሰረት በምክር ቤቱ ጅምር የሥራ እንቅስቃሴ አንፃር ታሪካዊ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ ነሐሴ 15/1987 ዓ.ም የተመሠረተው የፌዴሬሸን ም/ቤት በወቅቱ ወንድ 101 ሴት 7 አባላትን በአጠቃላይ 108 የም/ቤት አባላት ነበሩት፡፡

 

 

 

/ቤቱ የፌዴራል መንግስት አባል ክልሎች የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካይ የሆኑ 108 አባላት ባካሄዱበት ስብሰባ የተግባር እንቅስቃሴውን ጀምሯል፡፡ የየክልሉ የብሔር ብሔረሰብና ህዝብ ውክልና ሲታይ ህገ-መንግስቱን መሠረት ያደረገና 58 ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተወከሉበት ነበር፡፡

በወቅቱ የነበረው የም/ቤቱ አባላት አመራረጥ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 61/3 መሠረት በየክልሉ /ቤቶች የተከናወነ እና የተወካዮች ብዛትም በአንቀፅ 61/2 መሠረት እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ በብሔርነቱ ወይም በብሔረሰብነቱ አንድ ተወካይ እና በተጨማሪ የብሔር ወይም የብሔረሰቡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል በፌዴሬሸን /ቤት ውስጥ ሊኖረው እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ ሕገ-መንግስት የፌዴሬሸን /ቤት በአንድ በኩል የአገራችን ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች የተቀዳጇቸው መብቶች ሳይሸራረፉ በተግባር እንዲተረጎሙ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በህዝቦች መካከል ያለው አንድነት በእኩልነትና በፅኑ መሠረት ላይ እንዲገነባ ለማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሸከመ /ቤት ነው፡፡

ለፌዴሬሸን /ቤት መመስረት አንደዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሰው ጉዳይ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከመገንጠል መብትን የተቀበለ እና፣ ህገ-መንግስቱ በህዝቦች ስምምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ የሕዝቦችን አንድነት ለማስጠበቅና ልዩነቶችም ከተከሰቱ በህገ-መንግስቱ መሠረት መፍትሔ በመስጠት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስር መስደድ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ነው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጀመሪያ ስብሰባው የተከፈተው በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር በክቡር አቶ ከማል በድሪ ሲሆን በወቅቱ በምክር ቤቱ አሰራርና የስብሰባ ስነ ስርዓት ደንብ የዋና አፈጉባኤ አመራረጥ አንቀፅ 51 መሠረት ከተጠቆሙት ሁለት እጩዎች / አልማዝ መኮ ከኦሮምያ ክልል በዋና አፈጉባኤነት፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ለምክትል አፈ ጉባኤነት ከተጠቆሙት ሁለት አጩዎች አቶ ዚያድ በድሪ ከሶማሌ ክልል ሲመረጡ  ምክትል አፈ-ጉባኤውን ክልሉ ስለሳባቸው (ሰለፈለጋቸው) ምክር ቤቱ ሚያዝያ 3/1989 .. ባካሄደው ስብሰባ በምትካቸው የተከበሩ / መሀመድ ሰርሐዬን በመምረጥ ተተክተው እንዲሰሩ ተደርጓል እንዲሁም /ቤቱ በመስከረም 28/1995 .. መደበኛ ስብሰባው በወ/ አልማዝ መኮ ምትክ ክቡር / ሙላቱ ተሾመን በዋና አፈ-ጉባኤነት መርጧል፡፡ ምክርቤቱ የተጣለበትን ሃላፊነቶች ለመወጣት ያስችለው ዘንድ፤ ከመስከረም 1993.. ጀምሮ ሦስት ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል እያንዳንዳቸው አስራአንድ አስራአንድ አባላት የነበሩአቸውን እነዚህ ኮሚቴዎች (1) የህግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ (2) የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ (3) የክልል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴን አደረጃጀቶች እንደገና በማየት መስከረም 26-27/1996 .. እያንዳንዳቸው አስራአምስት አስራአምስት አባላት ባላቸው ሁለት ኮሚቴዎች (1) የበጀት ድጐማና የገቢዎች ክፍፍል ቋሚ ኮሚቴ (2) የህገ-መንግስት የክልል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚል በሁለት እንዲጠቃለሉ ተደርጓል፡፡

ከዚህ ሌላ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 82 መሠረት አስራአንድ አባላት ያሉት የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በማደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮችን የማጣራትና በፌዴራሉና በክልል ህግ አውጪ አካላት የሚወጡ ህጐች ከህገ-መንግስቱ ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳ ጉዳዩን በመመርመር ሕገ-መንግስታዊ ትርጉም በመስጠት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻው ውሳኔ እንዲሰጥበት በማድረግ ሰፊ ተግባራት ተከናውናዋል፡፡ በእስካሁን የምክርቤቱ ቆይታ ከፍተኛ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በህገ-መንግስቱ መሠረት በአወካከሉ የተወሰኑ መስተካክሎች ተደርገዋል፡፡

በዚህ መሠረት የፌ//ቤት እስከ አሁን ባለው አወካከል ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል 46 ብሔረሰቦች የም፣ ዳውሮ፣ አላባ፣ ደሰነች፣ ሐመር፣ ፀማይ፣ ጊዲቾ፣ ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አይዳ፣ ዘይሴ፣ ደራሼ፣ ማሽሌ፣ ኩስሜ፣ ገዋዳ፣ ኤርቦሬ፣ ቦዲ፣ ዲሜ፣ መኤኒት፣ ሽኩ፣ ዲዝ፣ ሙርሲ፣ ኮንሶ፣ ቤንች፣ ሀድያ፣ ኮሬ፣ ጉራጌ፣ ማርቆ፣ ቀቤና፣ ጐፋጋሞ፣ ወላይታ፣ ከምባታ፣ ኮንታ፣ ጠንባሮ፣ ሸክቾ፣ ከፍቾ፣ ጌድኦ፣ ሲዳማ፣ ሱርማ፣ ጫራ፣ ናኦ፣ ኛንጋቶም፣ ማሌ፣ አሪ፣ ዙልማም (ባሌ) 54 ተወካዮች የተወከሉ ሲሆን ኦሮምያ ክልል ከኦሮሞ ብሔረሰብ 19 ተወካዮች ከአማራ ክልል 17 ተወካዮች ያሉት የአማራ፣ የአርጐባ፣ የአገው እምራ፣ የአገው አዊ እና የኦሮሞ ብሔረሰቦችን ሲያካትት፤ ከትግራይ ክልል ስድስት ተወካዮች ያሉት የትግራይ፤ የኩናማ፣ የኢሮብ፣ ብሔረሰቦችን፤ ከጋምቤላ ክልል አምስት ተወካዮች ከአኙዋክ፣ ኑዌር፣ iንገር እና ኡፓ ሲወከሉ፤ የቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል አምስት ተወካዮች ከማኦ፣ ከጉሙዝ፣ ሺናሻ፣ ከበርታ ብሔረሰብ፤ ከሶማሌ ክልል አራት የሶማሌ ብሔረሰብ፤ ከሐረሪ ክልል አንድ የሐረሪ ብሔረሰብ፣ የአፋር ክልል ሁለት የአፋር ብሔረሰብ ተወካዮች የያዘው የፌዴሬሽን /ቤት በአጠቃላይ 67ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተወከሉበት 112 የምክር ቤት አባላት በመያዝ ሁለተኛውን የምርጫ ዘመን ተልእኮ በማጠናቀቅ ለሦስተኛው የምርጫ ዘመን የአምስት ዓመት የሥራ ጊዜ የየክልሉን ውክልና ባካተተ ህገ-መንግስቱን መሠረት ባደረገ ሁኔታ የበለጠ በመስራት ለውጤታማነቱ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

tomtop | homekit | JJPRO X5 | LEMFO LEM7 | Vernee T3 Pro | Anet | ILIFE V7s | koogeek | DJI Mavic Air | Hubsan Drone | Wltoys | Feiyu | Zeblaze | hubsan h501s | lixada | hohem gimbal